Friday, March 7, 2014

ግጥም - ዝናሽና ወጉ



 ጠላት ዘመድ አርጎ  ሊኖር አይወድም
አንገት ደፍቶ መኖር  አርጎት አያውቅም
ወልቃይት ጠጌዴ ባለ ጋንዴ ብረት ጥይቱ ጥምጥም
ኮስታራ አንበሴ  ያረጋል ግርድም።
       አገሬ ወልቃይት አገሬ ጠጌዴ  ሂዳቹሁ ብታዩት የሰርጉ እለት
       ለካ ብዙነው አይነቱ  ሰማንያ ሚሉት
       ወጉና ስራአቱ  አርጎ ሚያስደስት።
እንበል እንየው  ተባባሉ ውሪ
ባህል ወጉ ማስያዝ  ያስታጥቃል ሱሪ
ለልጆች ለማውረስ   እኛ ንሁን መሪ
ተረካቢው ትውልድ  ይሆናሉ አኩሪ።
       ደጋው ብትጎበኙት  ቆላው ብታዩት
       የከብቱ የበጉ  የበቅሎው ብዛት
       የማሽላ እሸቱን  የሰሊጥ ቅባት
       ትሉት ነበር ለአምላክ  እኔን ከርሳ ፊት
አገሬ ወልቃይት አገሬ ጠጌዴ  ዘላለም እሸት
ሁሌ ጮማቁርጥ  ሁሌ ማርና ወተት
እየመገበችናት  ኢትዮጲያን መሬት
ጎተራው ክምሩ  ይገድላል ስስት
ታዛቢው ባዕዱ  ቀልቡን እስኪስት።
      አገሬ ኢትዮጲያ  ደስ  ይበልሽ ደስ
      ዘወትር ይጠራ  ስምሽ ይታደስ
      መአዛሽ ጣፋጭ ነው  በሰሜን ሲነፍስ
      የጀግኖቹ ወኔ የምትከነክን ናት  የምታስነጥስ።
ቅቤ እንደ ጭቃ  የሚታፈስበት
ወተት በግሬላ   ጠትተን ያጠገብንባት
ሰሊጡ እንደአፈር   ሚገበይባት
አምላኬ አደራ   እሳን ጠብቃት።
       በሰሜን ኢትዮጵያ  ዘወትር ሚጠሩሺ
       አበጥሮ ዘሪ   ብለው የዘፈኑልሺ
       ማረሻው ምንሽር መጎንጎያው ጋንዴ   ብለው ሚያሞናሙኒሺ
       አገሬ ወልቃይታ አገሬ ጠጌዴ   አያልቅም ዝናሺ
ጀግንነት ጉብዝና  የለውም ብልሀት
አንድ ነገር ነበር  አባቶች ሚሉት
ዘርዋ ይታወቃል  ወልቃይቴ ሴት
ገና ከሽሉ ነው  የምታደሉት
ልናገር ልመስክር   ያኔ ያየሁት
ለወዳጅ ፊሪዳ  ለጠላት ጥይት።
       መጨካከን ይቅር  ሁሉም ያአንድ አገር ሰው
       እባክህ አምላኬ  ንፋሱን መልሰው
       ወንድሙን ወንድሙ   በልቶ ሳይጨርሶው።
እንደ እሸት ፈልፍለው   እንዱ ማርስርሰረው ይናገሩላት
አገሬ ወልቃይት አገሬ ጠጌዴ  የጀግኖች አናት
ገብሱና ጤፍ ቅቤ  ማሽላ ሰሊጥ የሚገኝላት
በሰሜን ኢትዮጵያ  የሐበሻ ገነት።
                ወንድሜ አትጨነቅ  እንዲሁ አትቸገር
                ኩነኔ እኮ አይደለም  እውነትን መናገር
                ይመስክር ማረሻው  ይመስክር ትራክተር
                ከድሮ እኮ ነው የወልቃይት እድር   የወልቃይት ማህበር።

                                                   በ.ሲሳይ.አ

ግጥም - ወጉና ትዝታው


    ወጉና ትዝታው

ጀሮዬ ንቁ ናት   የሩቅ ትሰማለች
የተፈራች አንበሳ   ትወልዳለች
የእድሬ አላማ   በአለም ላይ ታውቃለች።
      አገሬ ኢትዮጲያ   በጣም ሓብታም ነሺ
      ቡናውም ሰሊጡ ገብሱና ማሽላ  የሚበቅልብሺ
      የግዮን ውሃ  ተርፎሽ የሚፈስቢሺ
      ከአጽናፍ አስከ አጽናፍ   ሁሉም የሚያውቅሺ
      አምላኬ ፈጣሪ አንችነን ጠብቆ  በላይ ያኑሪሺ።
አሁን ልናገር   የእውነት ያየሁት
ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ  ትላለች ሜሬት
ለቅን ብንነሳ   ሁሌ በህብረት
ስም ማጥፋት ብናቆም  አሉት ከማለት
የሐበሻ እናት ኢትዮ  ነበርን ናሰኛት።
      እድር ጠቄሜታው ለኑራአችን ብቻ  የምትሉካላቹሁ
      እኔም ልንገራቹሁ  በጣም ተሳስታቹሁ
      ለነፍስም ጭምር ነው  የሚተርፍባቹሁ
      የተሳካ ኑሮ  ይሆናል ኑሮቹሁ።
ዘመድ ጥያቃ ህጄ  ከአንዱ ሲጫወት
እዱሩን አይረባም  ሲል ሰማሁት
እኔም አስረዳሁት  በደንብ ነገርኩት
ደግሜ እንዲያነበው  ደንቡ ሰጠሁት
አለኝ እኔም አሁኑ መግባቴ ነው  ከዚቺ እለት።
       ጥሪየን ስሙልኝ እንተባበር እንሁን በጋራ
       አትጨንቁበት ቢወራ ቢወራ
       እንደ ጉም ይጠፋል የሴረኞች ሥራ።
አትጠላኝም ቢየ ነው  ወገኔ ያልኩህ
እኔ እኮ አውቃለሁ  ምን እንደሚሉህ
ይቆርቁርህ ነበር  እኔ ባልነግርህ
እያሳሰበኝ ነው  እንዲህ ከቀረህ።
       ዘመን ተለውጦ  መስከረም ሲደርስ
       በሜልበርን ከተማ  ይነፍሳል ንፋስ
       ወገን በማግኘቱ  ስንቱን አለው ደስ
       ስትመኘው ነበር  የልብህ ሲደርስ
       እልልታው አሽካካው   ሁልም እርስበርስ።
እድሩ ተግባሩ ያሰኛል ቅዱስ
ወደዱት ደገፉት ከቄስ ተጳጳስ
እንግዲህ ነግረናል  እንዳንወቀስ
ለነገሩ አይሰማም  ጥፋያለው ነፍስ።
       ወልቃይት ጠገዴ ዝናዋ አያልቅም  ቢነገር ቢወራ
       ከአበው የወረስነው  መጨፎው ውጅግራ
       ሁላችን እንጻፈው  እዳንረሳ አደራ።
የጥንቱ አባቶች  በሰርግ ሲመርቁ
ተጠርተው ተገኝተው  ከበሉ ካበቁ
ክበሩ ውለዱ  ሰይሙት ታምሩ
ጠበቃ ሊሆናት  ለኢትዮጲያ ሀገሩ።
      ከኝህ መሽሮች  የሚወለድ ልጅ
      ለአገሩ ይጠቅማል  ለወገን ሚበጅ።
ግድየለም እኔ ልንገራቹሁ  አትጠራጠሩ
ትጥቃቸው ዝናቸው  መልካቸው የሚያምሩ
ወልቃይት ጠገዴ   ብላቹሁ ንገሩ።
      ወዬልህ ወልቃይት  ወዬልህ ጠገዴ
      አባትህ አትርሳ  እንዳትል ለሆዴ
      ነግረውን አልፈዋል  አየዋና ክንዴ
      ስማኝ ግድየለህም  ሌላማንምየለኝ አንተ ነህ ዘመዴ። 
ውላችን ምንድን ነው  እኛም አንጎትኛ እናንተ አንጎትኛ
ታዲያ ምን መጣብን  ማንስማማ እኛ 
ቂም በቀል አርቀን   እንድንሆን ጋደኛ
እባክህ አምላኬ   አጥፋልን ምቀኛ
ለኔ ማለት ትተን   ልንል ለኛ ለኛ።
        እስቲ አንጎትኛ   ይኖር ይሆን ዛሬ
        ወንድም ሴቱም ሁሉ   ሲታጠቁት ሱሬ
        መኖር ትኖራለች   በአንዳንዱ ገጠሬ።
እድሬ ህይወቴ   እያልኩኝ ባልናገር በአፌ
የእድሬን አላማ   በእጄንን አቅፌ
ፊቴን እያጠበኩኝ  እንዳይመጣ እንቅልፌ
አይገርማቹሁም ወይ   እናንተን ማትረፌ
        ከአንዳንድ ጋር ሁነን   እኔም እየው ስለው መልሶ ይለኛል
        እሱነን ሲነሳ በጣም  ደስ ይለኛል
       ወልቃይት ጠገዴ  ገባሁ ይመስለኛል።
ጳጳስ ያሉቱን   እኔ ልንገራቹሁ
የተባረከ እና   ቅዱስ ነው ስራቹሁ
ለአገሩ የሚጠቅም  ሰው ይውጣላቹሁ።
       ሸኽ ኡመርም ጭምር  እንዲህ ነው ያሉት
       አሰላም አሌይኩም  በውጭም በቤት
       ስማቹህ ያስፈራል  በሩቅ ሲጠሩት
       አላህ ይጨመረው   ለምታረጉት።

                                  
                               በ.ሲሳይ.አ